ቍጥር ፱/፳፻፮ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ።

ቃለ ዐዋድ!
እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።

የአዋጅ ቃል!
ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

ስለእግዚአብሔር እም ማንነትና ምንነት ዝክረ ነገር።

ከሰባቱ ቅዱሳት ኪዳናት መካከል፡ የመጀመሪያዎቹ ሦስቱ እና ሰባተኛው የኾነው፡ ኪዳነ ምሕረቱ ሳይጨመር፡ በተለይ፡ በመካከለኛው፡ በኪዳነ ኦሪት ዘሥጋ የተጠቃለሉት፥ "ኪዳነ አብርሃም፥ ኪዳነ ሙሴ እና ኪዳነ ዳዊት" የተባሉት፡ የኋለኞቹ ሦስቱ፡ ለእስራኤል ልጆች የተሰጡ መኾናቸው፥ እነርሱ፡ የእስራኤል ልጆች ግን፡ እነዚህኑ፡ ሦስቱን ኪዳናት፡ አክብረው ሊፈጽሟቸው ባለመቻላቸው፡ ወደእናንተ፡ ወደኢትዮጵያ ልጆቼ ተመልሰው መጥተውና በእናንተ ዘንድ፡ በአደራ ተጠብቀው መኖራቸው፥ እናንተም፡ በትክክለኛው የእውነትና የመንፈስ ቅዱስ አምልኮ ሥርዓታችሁ፡ በምግባር ላይ ዐውላችሁ፡ ስትገለገሉባቸው መቆየታችሁ፡ በኹሉ ዘንድ የታወቀ እውነታ ነው።

እነዚህ፡ ሦስቱም ቃል ኪዳናት፡ የእያንዳንዳቸው ትንቢታዊ ጊዜ ሲደርስ፡ በእናንተው በኢትዮጵያ ልጆቼ ዘንድ፡ ለፍጹሙ ፍሬ የበቁ ሲኾኑ፡ በዛሬው የዐዋጅ ቃሌ፡ አበክሬ የምነግራችሁ ግን፡ በተለይ፡ ኪዳነ ሙሴ የተገለጠባትን፡ የ"ታቦተ ጽዮን"ን ትእምርተ ሓተታና ዝክረ ነገር በሚመለከት ይኾናል።

ይኸውም፡ የእኔ የእናታችሁ የቅድስት ድንግል ማርያም፡ በሊባኖስ ተራራ ላይ የመወለዴ መታሰቢያ፡ በእናንተ በቃል ኪዳን ልጆቼ ዘንድ ከሚከበርበት፡ ከግንቦት ፩ ቀን ጀምሮ፡ እስከግንቦት ፲፮ ቀን ድረስ ባሉት ዕለታት፡ በተለይ፡ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ እና ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ለኾንሁት፡ ለእኔ፡ ለእግዚአብሔር እም (ለእናቲቱ እግዚአብሔር) ድንግል ማርያም፡ ቀዳሚ ምሳሌዬ ኾና ስለቆየችው፡ ስለታቦተ ጽዮን ምንነትና ማንነት፡ እኔ የምሰጣችሁ ማብራሪያ ነው።

መልእክቱን፡ በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...