ቍጥር ፲፩/፳፻፮ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ።

ቃለ ዐዋድ!
እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።

የአዋጅ ቃል!
ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

የእግዚአብሔር ሰላም ስንል ምን ማለታችን ነው?
እውነተኛዋ የእግዚአብሔር ሰላም የሰብአዊው ፍጥረት መጀመሪያ ከሆኑት፡ ከአዳምና ሔዋን ህልውና አንሥቶ እስከዛሬ ለዘለዓለምም በቅዱሱ ኪዳን አማካይነት ለሰው ልጆች ኹሉ ተሰጥታለች ነገር ግን ተጠብቃ የኖረችው፡ በኢትዮጵያውንና በኢትዮጵያውያት ዘንድ ብቻ መሆኑን በተመለከተ።

ይዤላችሁ የመጣሁት፡ የዐዋጅ መልእክቴ፡ በአንድ ወገን፡ እናንተ፡ ጥቂቶቹ ሰብኣውያን ፍጡሮቻችን፡ "የእግዚአብሔር እና የኢትዮጵያ ልጆች" ተብላችሁ፡ ዛሬ፡ በዚህ ዓለም፡ በምድር ላይ፡ በሥጋዊው አካልና ባሕርይ ሣላችሁ፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ፡ በአንድነት እየኖራችሁት ያላችሁት፡ የሰላምና የፍቅር፥ የደስታና የብልጽግና ሕይወት፡ ምን ዓይነት እንደኾነ፥ በሌላው ወገን ደግሞ፡ "የክፉውና የሰው ልጆች" ተብላችሁ በመጠራት፡ እየራሳችሁን፡ ለዚያ የብፅዕና ሕይወት ላላበቃችሁት፡ ለብዙዎቻችሁ ሰብኣውያን ፍጡሮቻችን ኹሉ፡ እርግጡን፡ አጕልቶና አግዝፎ የሚያሳያችሁ እውነታ ነው።

ያም እውነታ፡ ከእናንት ልጆቻችን መካከል፡ አንዱ በኾነው፡ በዛሬው ኢትዮጵያዊ አገልጋያችን፡ በኪዳናዊው ኤርምያስ በኩል፡ ከዚህ አስቀድሞ፡ "ጾመ ኢትዮጵያ"ን እና "ሰላም ለኢትዮጵያ"ን በሚመለከት፡ እንዲተላለፍላችሁ ስናደርግ በቆየነው፥ እኔም፡ አኹን፡ ያን በማዘከርና በማጠቃለል፥ በማጽናትና በማደስ በማቀርብላችሁ፡ በዚህ፡ የምሥራች መልእክታችን አማካይነት የሚከሠተው ነው።

ይኸው የምሥራች መልእክታችን፡ በ፳፻ (በ፪ሺ) ዓመተ ምሕረት፡ ለጥቂት ጊዜ የተፈታው ዲያብሎስ፡ በተለይ፡ ከዚያ ወዲህና በዚህ፡ በ፳፻፰ተኛው (፪ሺ ስምንተኛው) ዓመተ-ምሕረት፥ ወደፊትም፡ የሚያስከትልበትን የፈተናና የችግር ማዕበል፡ በድል አድራጊው ኢትዮጵያዊው አንበሳ፡ ልጄ ወዳጄ፡ ኢየሱስ መሢሕ፥ ከእርሱ አስቀድሞም፡ እጆቼን፡ ምንጊዜም፡ ወደእርሱ፡ ወደእግዚአብሔርነታችን በዘረጋሁት፡ በእኔ፡ በኢትዮጵያዋ ቅድስት እናቱ ድንግል ማርያም፡ የቃል ኪዳን ኃይል፡ ይህ፡ ኢትዮጵያዊው ኪዳናዊ ትውልዴ፡ እስከዛሬ፡ በየዓመቱ፡ ሲያካኺድ በቆየው፡ በ"ጾመ ኢትዮጵያው" እና በ"ሰላመ-ኢትዮጵያው" ምሕላ አማካይነት፡ ለመቋቋምና ለማስወገድ ስለቻለበት መፍትሔ፡ የሚናገረው ቃላችን ነው።

ጥያቄዎችና፡ መልስ ኾነው የተጠቃለሉት ዓበይት ቍም-ነገሮች
፩ኛ. የአርባ ዓመታት ምሕላና ሱባኤ ፍሬ።
፪ኛ. "ጾመ ኢትዮጵያ"ን በሚመለከት።
፫ኛ. በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ዘንድ፡ የሰላም ምንነትና ማንነት።

መልእክቱን፡ በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...