ቍጥር ፲፮/፳፻፱ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ።

ቃለ ዐዋድ!

እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።

የአዋጅ ቃል!

ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

ግዝረትን፡ እንዲሁም፡ በእጮኛነት፥ ልጄን ወዳጄን እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕንም፡ ከፅንሰቱና ከልደቱ፥ በጠቅላላም፡ ከሕፃንነቱ ጀምሮ፡ በፍጹም ቅንነትና ታማኝነት ያገለገለንን፡ ባለሟላችንን፡ ጻድቁ ዮሴፍን፥ በዚህ ተልእኮ፡ ከእርሱ ያልተለየችውን፡ የቅርብ አገልጋያችንን፡ ሰሎሜን ጭምር በሚመለከት።

በቅዱሱ ኪዳን የኢትዮጵያ ልጆቼ ዘንድ ታውቃና ታምኖባት የኖረች፡ ማንኛውም ዓይነት ተቃዋሚ ኃይል፡ መንፈሳዊዉም ኾነ፥ ሥጋዊው፡ በተቃዋሚነት፡ ሊቋቋማት፣ በተፃራሪነትም ሊያስወግዳት ያልቻለ፥ የማይችልም፡ የእኛ፡ የእግዚአብሔር እውነት አለች። ነገር ግን፡ በዚህ ረገድ ያለችው፡ ይህችው፡ የእኛ፡ የእግዚአብሔር እውነት፡ ልጄን ወዳጄን እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕን እስከመግደል በደረሰ ጥላቻና ተቃውሞ፡ እስከዛሬ እያሳደዱት ባሉት፡ በአይሁድ ዘንድ፡ ለ፫ሺ፱ ዓመታት፥ ይልቁንም፡ ግብረ-ዐበሮቻቸው በኾኑት፡ በግብፅ ኦርቶዶክሳውያን መነኮሳት ደግሞ፡ ለ፩ሺ፮፻፱ ዓመታት፣ "ኢትዮጵያዊ ነኝ!" እያለ፡ በስሜ ከሚጠራው፡ ከዚህ፡ ከከሃዲውና ከዓመፀኛው፥ ከአመንዛሪውና ከክፉው ትውልዴ ዘንድ፡ እንዲህ፡ በሓሰቱ አበጋዝ፡ በዲያብሎስና በአገልጋዮቹ የክፋት ሠራዊት፡ ተዳፍናና ተገልላ እንድትኖር በመደረጉ፡ እነሆ፡ ለረዥም ዘመናት፡ ተደብቃና ተሠውራ፥ ማስናና ምስጢር ኾና፡ ሳትከሠት ቆይታለች።

ዛሬ ግን፡ በዚህ ረገድ ያለችውን፡ ይህችኑ፡ የእኛ የኾነችውን፡ የእግዚአብሔርን እውነት፡ ልጄ ወዳጄ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕ፡ በንጉሥነቱ፥ እኔም፡ እግዝእተብሔር እም፡ ድንግል ማርያም፡ በንግሥትነቴ፡ በገሃድ እና በቀጥታ በምንመራት፡ በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥታችን አማካይነት፡ እኔው ራሴ፡ በዚህ፡ የዐዋጅ ቃሌ፡ ይፋ አውጥቼ፡ ለመላዎቹ ፍጡሮቻችን፥ በተለይም፡ በቅዱሱ ኪዳን ላገኘኋችሁ፡ ለእናንተ፡ ኪዳናውያን ኢትዮጵያውያንና ኪዳናውያት
ኢትዮጵያውያት፡ የቃል ኪዳን ልጆቼ፡ ልገልጽላችሁ የሚያስፈልግ ኾኖ በመገኘቱ፡ ይኸው፡ ስለዚችው የእግዚአብሔርን እውነት፡ እያናገርኋችሁ አለሁ፤ እናንተም፡ እነሆ፡ እየሰማችሁኝ አላችሁ።

ጥያቄዎችና፡ መልስ ኾነው የተጠቃለሉት ዓበይት ቍም-ነገሮች
፩ኝ. በግዝረት ምልክትነት የተገለጠውና ጸንቶ የኖረው ኪዳነ-አብርሃም
፪ኛ. የኢየሱስ መሲሕ ግዝረት
፫ኛ. የ፩፻፵፬ሺ ሕፃናት የመሥዋዕትነት ደም፡ በሄሮድስ እጅ እንዲፈስስ፡ ለምን አስፈለገ?
፬ኛ. አይሁድ፡ የእግዚአብሔርን ሥርዓት አፍራሽነታቸው
፭ኛ. የአብርሃም ግርዛት ለምን አስፈለገ?
፮ኛ. ሰዎች ሊያማስኑት የሞከሩት፡ ቅዱሱ እጮኛማነት
፯ኛ. የድንግል ማርያም እጮኛ፡ የጻድቁ ዮሴፍ፡ ጃንደረብነት እና ድንግላዊነት

መልእክቱን፡ በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...