የ፪ሺ፰ (፳፻፰) ዓመተ ምሕረት፡ የዓውደ ዓመቱ: ምሥራች መልእክት።

ልዑል እግዚአብሔር፡ ከዘመነ ሉቃስ ወደዘመነ ዮሓንስ አሸጋግሮ፡ የ፯ሺ፭፻፰ (የሰባት ሽህ አምስት መቶ ስምንት)ኛውን ዓመት፡ የነጻነት ሕልውናችንን በዓል፥ ይልቁንም፡ የእግዚአብሔር እም ድንግል ማርያምን፡ የ፪ሺ፳፬ (የኹለት ሽህ ሃያ አራት)ኛውን ዓመት፡ እና የእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስን፡ የ፪ሺ፰ (የኹለት ሽህ ስምንት)ኛውን ዓመት፡ የልደታት በዓል ለማክበር ለበቃንበት፡ ለአዲሱ የ፪ሺ፰ (፳፻፰) (ኹለት ሺህ ስምንት፥ ወይም ሃያ መቶ ስምንት፥ ወይም፡ ዕሥራ ምዕት ወሰምንቱ) ዓመተ ምሕረት፥ መስከረም ፩ ቀን፣ ደግሞም፡ ለፍጥረተ-ዓለሙ ባለው ፍጹም ፍቅሩ፡ በተቃዋሚው የክፋት ኃይል ፊት፡ እንደበግ ተሠውቶ፥ እንደአንበሳ፡ በድል አድራጊነት የተነሣው፡ የቤዛችን፡ የኢየሱስ መሢህ፡ የግዝረቱ፥ የዕፀ መስቀሉና የደመራው፥ የበዓተ መቅደሱና የስደቱ በዓላት፥ ከእነዚህም ጋር ተያይዞ ለሚደርሰው፡ የፍጥረተ ዓለሙ መድኃኒትና እናት ለኾነችው፡ ለቅድስት ድንግል ማርያም፡ የፍልሰተ ዕርገቷ በዓል፡ እንኳን፡ በያለንበት፡ በሰላም አደረሰን!

+++

መልእክቱን በሙሉ ለመመልከት፡ እንደሚከትለው ይቀጥሉ!...