የ፳፻፯ ዓ.ም. የፍልሰታ ማርያም በዓል መልእክት።

አግሃደት ፍልሰታሃ፡ ማርያም ድንግል!
በከመ ትንሣኤ ወልዳ፡ ዘልዑል!

ድንግል ማርያም፡ ፍልሰቷን ገለጠች!
የልጇን ትንሣኤ፡ በእርሱ አጸደቀች!

+ + +

ልዑል እግዚአብሔር፡
ሃይማኖታችንና አገራችን፥ እናታችንና ንግሥታችን፡
እግዚአብሔር እም፡ ቅድስት ድንግል ማርያም፡
ከምድር ወደሰማያት የገባችበትን፡ የፍልሰቷን በዓል፡
ዘንድሮም፡ በ፳፻፯ተኛው (ኹለት ሽህ፡ ሰባተኛው) ዓመተ-ምሕረት፡
በያለንበት፡ በደኅና አድርሶ፡
እንኳን፡ በሰላም ለማክበር አበቃን!

+ + +

ፍልሰታሃ ለማርያም!

ድንግል ማርያም፡
በመለኮታዊና ትስብእታዊ የተዋሕዶ ኹለንተናዋ፡
ወደሰማያት የመውጣቷ ትንግርት!

ሰማያዊ ልዕልና፡ ዘበዓለ ፍልሰታ ለማርያም።

ነሓሴ ፲፮ ቀን የሚከበረው፡
የቅድስት ድንግል ማርያም፡ ወደሰማይ የመፍለሷ በዓል።

[የግእዙ ቃል "መሢሕ"፡ በግሪክኛ፡ "ክርስቶስ" ይባላል።]

     "ፍልሰታሃ ለማርያም!" በሚል ስያሜ፡ ነሓሴ ፲፮ ቀን የምትከበረው፡ የቅድስት ድንግል ማርያም፡ የፍልሰቷ መታሰቢያ በዓለ ዕለት ዝክረ ነገር፡ እንዲህ
ነው፦
     "ወልደ አብ ፡ ወልደ ማርያም"፡ "የአብ ልጅ ፡ የማርያም ልጅ" የኾነውና የተባለው፡ ኢየሱስ መሢሕ፡ የመለኮትና የትስብእት ወላጆቹ ከኾኑት፡ ከእግዚአብሔር አብ አባቱ እና ከእግዚአብሔር እም ድንግል ማርያም እናቱ፡ እንዲህ ተወልዶ፥ እርሷ፡ ቅድስት እናቱም፡ በመስቀሉ ሥር ሳይቀር በመቆም፡ ለአንዲት ቀን እንኳ ሳትለየው፡ ዲያብሎስንና የክፋት ሠራዊቱ የኾኑትን፡ ርኵሳን መናፍስቱንና ሰብኣውያን ግብረ ዐበሮቹን፡ በመሥዋዕትነትና በቤዛነት የፍቅር ኃይል፡ ከ፴፫ ዓመታት በላይ ለኾነ ዕድሜ በመዋጋት፡ በመጨረሻ፡ ኹሉንም፡ በድል አድራጊነት አሸንፎ፡ ከምድረ ገጽ አስወገደ።

መልእክቱን በሙሉ ለመመልከት፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...