የ፳፻፲ ዓ.ም. የፍልሰታ ማርያም በዓል መልእክት።

የ፳፻፲ ዓ.ም. የፍልሰታ ማርያም በዓል መልእክት።

ነሓሴ ፲፮ ቀን የሚከበረው፡ የቅድስት ድንግል ማርያም፡ ወደሰማይ የመፍለሷ በዓል።
[የግእዙ ቃል "መሢሕ"፡ በግሪክኛ፡ "ክርስቶስ" ይባላል።]

"ፍልሰታሃ ለማርያም!" በሚል ስያሜ፡ ነሓሴ ፲፮ ቀን የምትከበረው፡ የቅድስት ድንግል ማርያም፡ የፍልሰቷ መታሰቢያ በዓለ ዕለት ዝክረ ነገር፡ እንዲህ ነው፦

"ወልደ አብ ፡ ወልደ ማርያም"፡ "የአብ ልጅ ፡ የማርያም ልጅ" የኾነውና የተባለው፡ ኢየሱስ መሢሕ፡ የመለኮትና የትስብእት ወላጆቹ ከኾኑት፡ ከእግዚአብሔር አብ አባቱ እና ከእግዚአብሔር እም ድንግል ማርያም እናቱ፡ እንዲህ ተወልዶ፥ እርሷ፡ ቅድስት እናቱም፡ በመስቀሉ ሥር ሳይቀር በመቆም፡ ለአንዲት ቀን እንኳ ሳትለየው፡ ዲያብሎስንና የክፋት ሠራዊቱ የኾኑትን፡ ርኵሳን መናፍስቱንና ሰብኣውያን ግብረ ዐበሮቹን፡ በመሥዋዕትነትና በቤዛነት የፍቅር ኃይል፡ ከ፴፫ ዓመታት በላይ ለኾነ ዕድሜ በመዋጋት፡ በመጨረሻ፡ ኹሉንም፡ በድል አድራጊነት አሸንፎ፡ ከምድረ ገጽ አስወገደ።

መልእክቱን በሙሉ ለመመልከት፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...