ቍጥር ፯/፳፻፮ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ።

ቃለ ዐዋድ!
እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።

የአዋጅ ቃል!
ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

የወሊድ ቍጥጥርን በተመለከተ።
የወሊድ ቍጥጥርን ከቶ ምንድር ነው? የእግዚአብሔር፥ ከእግዚአብሔርና ለእግዚአብሔር ነወይ?

በዚህ አዋጅ የማሰማችሁ ቃሌ፡ ‘የወሊድ ቍጥጥር›› ተብሎ፡ ከአሕዛቡ ዓለም መንጭቶ፡ ‹ሕዝብ› በተባላችሁት የፈጣሪ ወገኖች ዘንድ፥ በተለይም፡ ‹ክርስቲያን ነን›፣ ‹ቤተ ክርስቲያንም ነን›፣ ይልቁንም፡ ‹ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ነን› በምትሉት ልጆቼ ዘንድ ሳይቀር፡ ተስፋፍቶ ስለተሠራጨው፡ ሰብኣዊና ባዕድ ስለኾነው የኑሮ ፈሊጥ፡ በኪዳናውያንና በኪዳናውያት የኢትዮጵያ ልጆች በኩል፡ እየቀረበ ላለው ጥያቄ፡ መልስ የኾነውን መለኮታዊ ሥርዓት የያዘው መልእክት ነው።

በቅድሚያ፡ በነፍስ፥ በሥጋና በመንፈስ ተመሥርቶ፥ ተገድግዶና ተደምድሞ፡ በሕያውነት በቆመው፡ በእያንዳንዳችሁ የተፈጥሮ አካላዊና ባሕርያዊ ሰውነታችሁ ውስጥ ባለው፡ በቅዱሱ ኪዳን የኢትዮጵያዊነት ተዋሕዶ ሃይማኖታችሁና ምግባራችሁ፥ ሥርዓታችሁና ህልውናችሁ መነጽር፡ ጠልቃችሁ ልትመለከቱት፥ ልትመረምሩትም ይገባችኋል። በነፍስ አስተሳሰብ፥ በሥጋ አመለካከትና በመንፈስ ተመስጦ እየታየና እየተገመገመ እንደሚወሰነው፡ እንደማንኛውም ዓይነት ጽንሰ አሳብ፥ ወይም፡ ተግባራዊ አሠራር እና/ወይም ሚዛናዊ ፍርድ ኹሉ ማለት ነው።

ቀጥሎ፡ በኃይለኛውና በረቂቁ የመንፈስ ቅዱስ እሳት ምድጃችሁ፡ አቅልጣችሁና አንጥራችሁ በማውጣት፥ ፍጹም ፍትሓዊና ርትዐዊ በኾነው መለኮታዊ የፍርድ ሚዛናችሁም አጣርታችሁ፡ እውነተኛ ገጽታውን በማቅረብ፡ የእያንዳንዳችሁን ውሳኔ፡ በእየራሳችሁ ልትሰጡ ይጠበቅባችኋል።

ጥያቄዎችና፡ መልስ ኾነው የተጠቃለሉት ዓበይት ቍም-ነገሮች
፩ኛ. ቅዱሱ ኪዳን፡ ስለወንድ ዘር እና ስለሴት ወርኀዊ አበባ የሚለው።
፪ኛ. ቅዱሱ ኪዳን፡ በምትሓታዊው የኃጢኣት ቀንበር ለሚሥቃዩ፡ ያለው ምክር።
፫ኛ. ቅዱሱ ኪዳን፡ ስለጋብቻና ስለሩካቤ ሥጋ፡ ለትውልዱ የሚለው።
፬ኛ. ቅዱሱ ኪዳን፡ ስለጋብቻ መሠረታዊ ዓላማ የሚለው።

መልእክቱን፡ በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...