Faith

ጸሎተ ሃይማኖት፡ ዘኢትዮጵያ።

ንሕነ፡ ደቂቀ ኢትዮጵያ፦

ነአምን፡ በአሓዱ አምላክ፤ እግዚአብሔር ጸባዖት፤ አኀዜ ኵሉ፤ ገባሬ ሰማያት ወምድር፤ ዘያስተርኢ፥ ወዘኢያስተርኢ።

ወነአምን፡ ከመ አሓዱ እግዚአብሔር ጸባዖት፡ ረሰየ ዋሕድናሁ ፍጹመ፡ በክዕበተ ህልውናሁ ዘእግዚአብሔር አብእም፣ ዘኮነ፡ በሥርዓተ ሰብሳብ መለኮታዊ።

የኢትዮጵያ: የሃይማኖት ጸሎት።

እኛ፡ የኢትዮጵያ ልጆች፦

አንድ አምላክ በሚኾን፡ በአሸናፊው እግዚአብሔር  እናምናለን። 

እርሱም፡ ኹሉን የያዘው፣ ሰማይንና ምድርን፥ የሚታየውንና የማይታየውንም የፈጠረው ነው።

አንድ አምላክ የኾነው፡ አሸናፊው እግዚአብሔር፡ ይህን አንድነቱን፡ እርሱ በሠራው፡ በመለኮታዊው የጋብቻ ሥርዓት፡ በእግዚአብሔር አብእም ኹለትነት፡ ፍጹም እንዳደረገው እናምናለን።

ጸሎተ ኪዳነ ቃል፡ ዘኢትዮጵያ።

ንሕነ፡ ደቂቀ ኢትዮጵያ፦

ነአምን በኢትዮጵያውናነ፡ ዘኪዳን ቅዱስ፥ ህልው በዓቂበ ቃላት ኪዳናውያት፥ እለ ወሀቦን እግዚአብሔር፡ ለውሉድ ወአዋልድ፡ ዘሰብእ።

የኢትዮጵያ፡ የቃል ኪዳን ጸሎት።

እኛ፡ የኢትዮጵያ ልጆች፦

እግዚአብሔር፡ ለሰው ልጆች፣ ለወንዶቹም፥ ለሴቶቹም፣ የሰጣቸውን ቃል ኪዳናት፡ ጠብቆ በኖረው፡ በቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያዊነታችን እናምናለን።

አምላካችን፡ ይህን የኢትዮጵያዊ እና የኢትዮጵያዊት ሕያው ሰውነት፡ በመጀመሪያው የፍጥረት ዘመን፡ በአዳምና ሔዋን ሥርዓተ ጋብቻ፡ በኪዳነ ልቦና መሠረተው፤

ጸሎተ ስባሔ ለእግዚአብሔር።

ዘደቂቀ ኢትዮጵያ።

ኦ አቡነ፥ ወእምነ፥ ወእኅትነ፥ ወእኁነ፥ ወመንፈስነ እግዚአብሔር! ነአኵተከ እግዚኦ፥ ወንሴብሓከ፤ ንባርከከ እግዚኦ፥ ወንትአምነከ፤ ንገኒ ለከ እግዚኦ፥ ወንትቀነይ ለስምከ ቅዱስ፤ ንሰግድ ለከ፤ ኦ ዘለከ! ይሰግድ ኵሉ ብርክ፤ ወለከ ይትቀነይ፡ ኵሉ ልሳን።

አንተ ውእቱ፡ አምላከ አማልክት፤ ወእግዚአ አጋእዝት፤ ወንጉሠ ነገሥት። አምላክ አንተ፡ ለኵሉ ዘሥጋ፤ ወለኵላ ዘነፍስ።

የኢትዮጵያ ልጆች፡ ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት፡ የምስጋና ጸሎት።

አባታችንና እናታችን፥ እኅታችንና ወንድማችን፥ መንፈሳችንም፡ እግዚአብሔር ሆይ!

አቤቱ እንቀድስሃለን እናመሰግንሃለንም፤ አቤቱ እናወድስሃለን፤ እንታመንብሃለን፤ አቤቱ እናገንሃለንም፤ ለቅዱስ ስምህ እንታዘዛለን፣ እንሰግድልሃለን፤ ጕልበት ኹሉ፡ ለአንተ ይሰግዳል፤ አንደበትም ኹሉ፡ ወደአንተ ይጮሃል።

አንተ፡ የአማልክት አምላክ ነህ፤ የገዢዎች ገዢ ነህ፤ የንጉሦችም ንጉሥ ነህ። አንተ፡ የሥጋዊው ኹሉ፥ የነፍሳዊዉም ኹሉ ወገን ፈጣሪ ነህ።

ጸሎተ ሱላሜ፡ ለድንግል ማርያም።

ዘደቂቀ ኢትዮጵያ።

ኦ እግዝእተብሔር ማርያም እምነ፥ ወመድኃኒትነ!

ንብለኪ፡ "ሰላም ለኪ!" በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ።

ድንግል በመንፈስኪ፣ ወበነፍስኪ፣ ወበሥጋኪ። ይደልወኪ ዝ ሱላሜ፣ እስመ አንቲ፡ እሙ ለእግዚአብሔር ጸባዖት፡ በእንተ ዛቲ ንጽሓ ባሕርይኪ።

አንቲ ይእቲ፡ ሔዋን ቅድስት፤ ወቡርክት፡ እምኵሎን አንስት፡ በእንተ ዘአሥረፀ ማሕፀንኪ፡ ፍሬሁ፡ ዘዕፀ ሕይወት፣ በዘውእቱ ኮነ፡ አዳምሁ ቅዱሰ።

የኢትዮጵያ ልጆች፡ ለድንግል ማርያም የሚያቀርቡት፡ የሰላምታ ጸሎት።

እናታችንና መድኃኒታችን እግዝእተብሔር ማርያም ሆይ!

በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ፡ "ሰላም!" እንልሻለን።

በመንፈስሽ እና በነፍስሽ፣ በሥጋሽም፡ ድንግል ነሽ። በዚህ የንጽሕና ባሕርይሽ፡ የአሸናፊው የእግዚአብሔር እናት ነሽና፡ ይህ ሰላምታ፡ ለአንቺ ይገባል።

THE ETHIOPIAN CREED

We, Children of Ethiopia, believe in One God Igziabher, Almighty, Who Possesses All, Maker of the Heavens and Earth, the Visible and the Invisible.

THE TESTIMONIAL OF THE ETHIOPIANS ON THE HOLY COVENANT

We, Children of Ethiopia, believe in our Ethiopianhood of the Holy Covenant that embodied and conserved the Seven Divine Covenants GOD Igziabher granted to humanity, men and women.

PRAYER OF THE ETHIOPIANS IN GLORIFICATION OF THE LORD

Our Father, Mother, Sister, Brother and Spirit, God Igziabher! We thank You, and praise

PRAYER OF THE CHILDREN OF ETHIOPIA IN EXALTATION OF THE HOLY MOTHER.

Our Goddess Mary The Mother and Saviour! With the Words of Greeting of the Angel Saint Gabriel, we Bow to You in Solemn Worship saying, “Hail, O Favoured One!” You are Virgin in Spirit, in Soul and in Body. Because of Your Perfect Chastity, You Became the Mother of the Almighty God Igziabher.

የአቡነ ዘበሰማያት እና ኦ ማርያም እምነ ዘበሰማያት፡ ጸሎታት፡ በሚመለከት።

በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡

የኪዳነ መንፈስ ቅዱስ፡ የአቡነ ዘበሰማያት እና ኦ ማርያም እምነ ዘበሰማያት፡
አጫጭር ጸሎታት።