News & Information

ዮም ፍሥሓ ኮነ!
በእንተ በዓለ ስደቶሙ፡
ለሕፃን ኢየሱስ መሢሕ፥ ወለእሙ ድንግል ማርያም!

ይድረስ፦ ለኪዳናውያትና ለኪዳናውያን የኢትዮጵያ ልጆች! ለሌሎቻችሁም፡ የምንባብ ታዳሚዎቻችን ኹሉ!

እኔ፡ ኪዳናዊ ወንድማችሁ፡ ንቡረ-እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ-ኢየሱስ፡ ኢትዮጵያዊ ሰላምታዬን፡ በያላችሁበት፡ በእግዚአብሔር ስም አቀርብላችኋለሁ!

"ለእንግሊዝ መንግሥታዊና ሃይማኖታዊ ተሓድሶ፡ ምክንያት የኾነው፡ የመካከለኛው ዘመን፡ የኢትዮጵያ ሥርዓተ መንግሥትና የሕዝቧ አኗኗር -  (ኢ) ዩቶፕያ - የትርጕም ሥራና የምርምር ማስታወሻዎች - እውነተኛው "ሕዳሴ" ወይም "ተሓድሶ"፡ ከምንታዌነት (Dualism)፡ ወደተዋሕዶ (Unity) የሚደረግ፡ ኹሉን አቀፍ ኅብረተሰባዊ የንስሓ ጕዞ መኾኑን የሚያሳይ፡ ተጨባጭ እና ታሪካዊ ማስረጃ" በሚል አርእስት፡ በኪዳናዊት መስከረም ለቺሣ ተደርሶ፡ በ፳፻፮ ዓመተ ምሕረት የታተመውንና በሥርጭት ላይ የሚገኘውን መጽሓፍ አነበብሁት።

ለክቡራትና ለክቡራን አንባቢዎቻችን፡
አጭር ማሳሰቢያ።

    በዚህ የኅዋ ገጻችን ላይ ሠፍረው የሚነበቡት ጽሑፎች ኹሉ፡ በግእዙና በኢትዮጵያኛው ቋንቋዎች ተከትበው የሚቀርቡ በሚኾኑበት ጊዜያት፡ ቃላቱና አኀዛቱ፡ በራሳቸው ፊደላትና ቍጥሮች ብቻ ተከናውነው መዘጋጀት እንደሚገባቸው፡ እሙን ነው። ይህን አመኔታ፡ ኢትዮጵያዊው፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ሥርዓት፡ አበክሮና አጠንክሮ ያመለክተዋል።

ይህ የምትመለከቱት፡ አዲሱ የኅዋ ሰሌዳ፡ በተለያዩ፡ እንደጭን መቀመሪያና የኪስ ስልክ ባሉ፡ የኅዋ ዐውታር አገልግሎት መስጫ መሣሪያዎች ላይ፡ ብቅዓትና ጥራት ባለው መልኩ፡ አገልግሎት እንዲሰጥ፥ እንዲሁም፡ በተለያዩ፡ የኅዋ ዐውታር መጐብኛዎችም ላይ፡ ኢትዮጵያኛ (ዐምሓርኛ)ውን ሆሄያት፡ ያለምንም ችግር፡ ለቅሞና አጣርቶ ማንበብ እንዲያስችል ተደርጐ፡ በዘመናዊ መልኩ የተዘጋጀና የተዋቀረ ነው።