በአንገታችን ዙሪያ ሊጠለቅ የሚገባውና ትክክለኛው ማተብ፡ ምን አይነት ቀለም ሊኖረው ይገባል?

እኛ የቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ በክርስትና ጥምቀታችን ጊዜ፡ በየአንገታችን ሊታሠርልን የሚያስፈልገው፡ በኖኅ አማካይነት፡ ከእግዚአብሔር፡ በቃል ኪዳን የተቀበልነውና የሰንደቅ ዓላማችንን ቀለማትን አዋሕዶ የያዘው፡ አረንጓዴ፥ ብጫና ቀይ ክር ማተብ ሊኾን ይገባል። ዳሩ ግን፡ ግብፃውያን፡ ያን፡ መለኮታዊ ሕያው ቅርሳችንን፡በእነርሱ፡ የባዕድ አምልኮ አረማዊነት ምልክታቸው ለውጠውት ይገኛል፤ ይኸውም፡እነርሱ፡ እስከዛሬ እየሠሩበት ባለውና ነጭ፥ ጥቁርና ቀይ በኾነው፡ በግብፃውያን ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማቸው ቀለማት መተካታቸው ነው።