እግዚአብሔር ማነው?

ከእርሱ በላይ ምንም ነገር የሌለ፤ ነገር ግን ኹሉን ነገር ያስገኘ፤ ወደርና ምሳሌ የሌለው፤ ፍጡር አሰቦ ሊደርስበት የማይችል፤ አንድ ረቂቅ ምሥጢራዊ ማዕከል፤ ምንጭና ኃይል ያለው የህልውና ባሕርይ ነው። ይህን የሚታየውንና የማይታየውን ግዙፉንና ረቂቁን፤ የሚንቀሳቀሰውንና የማይንቀሳቀሰውን፤ ሕያውንና ምውቱን ፍጥረት ኹሉ ከራሱ አስቦ የፈጠረ፤ በራሱ አግዝፎ የሠራና ለራሱ አዘጋጅቶ ያቀረበ፤ እርሱ ስለኾነ፤ “ፈጣሪ” ይባላል።

፩ኛ. በግዕዝ፡ “እግዚአ - ብሔር” ሲል፤ “የአገሪቱ፤ የሕዝቡና የመንግሥቱ ፈጣሪና አምላክ፤ ካህንና ንጉሥ” ማለት ነው።

፪ኛ. እግዚአብሔር የአንድነቱ ስም ሲኾን፤ “እግዚእ፡- አብ፡- ሔር” የሚለው ደግሞ የሦስትነቱን ስም ያመለክታል። ይኻውም ፍጥረቱን የፈጠረው ጌታ ወልድ፤ ከአባቱ፤ ከአብና ከሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለውን፤ የአንድነትና የሦስትነት ምሥጢር በማሳየቱ ይታወቃል።

ወደ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ለመመለስ ይኽን ይጫኑት