የ፳፻፲፫ ዓ.ም. የደብረ ታቦር (ቡሔ) በዓል መልእክት።

ለእኛ፡ ለቅዱሱ ኪዳን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡ ከዓበይት በዓሎቻችን፡ አንዱ የኾነው፡ በዓለ ደብረ-ታቦር የሚውለው፡ በነሓሴ ፲፫ ቀን በመኾኑ፡ ለጾመ ፍልሰታ ሱባዔ፡ ልዩ ምዕራፍ ኾኖ፡ በታላቅ መንፈሳዊ ተመስጦና ማኅሌት ይከበራል።

ይህ በዓል፡ ከመድኃኒታችን፡ ከእግዝእትነ [እግዝእተብሔራችን] እም፡ ድንግል ማርያም፡ በሰውነት የተወለደው፡ ሰላማችን እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕ፡ በዐጸደ ሥጋ፡ ዐብረውት ከነበሩት ደቀ መዛሙርቱ መካከል፡ ጴጥሮስንና ያዕቆብን፥ ወንድሙንም ዮሓንስን፥ በዐጸደ ነፍስ ካሉት ባለሟሎቹ ደግሞ፡ ሙሴንና ኤልያስን፡ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ በሚገኘው፡ "ታቦር" በተባለው፡ የወይራ ዛፍ ተራራ ላይ አምጥቶ፡ የባሕርይ አምላክነቱን በመግለጥ፡ ታማኞች አገልጋዮቹ፡ ሊያዩ የተመኙትን፡ እንዲያዩ፥ ሊሰሙ የተመኙትንም፡ እንዲሰሙ ያደረገበት ቸርነቱና ኃይሉ የሚዘከርበት ነው።

መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!..