ቃለ-ዐዋድ - Divine Proclamations

ቃለ ዐዋድ!

እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።

የአዋጅ ቃል!

ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

"መጽሓፍ ቅዱስ"ን በተመለከተ።

በአኹኑ ጊዜ፡ "መጽሓፍ ቅዱስ" የሚባለው፡ የቅዱሳት መጻሕፍት ስብስብ፣ በተለይ፡ ብሉያቱ፡ እውነተኞቹ የእስራኤል ልጆች ሳይኾኑ፡ ራሳቸውን፡ "የእስራኤል ልጆች" የሚሉት፡ ኦሪታውያኑ አይሁድ የጻፉት ስለኾነ፡ የኢትዮጵያ ልጆች መጽሓፍ አይደለም። ይህም እውነታ፡ የገናናዎቹ እና የስመ-ጥሩዎቹ፡ የእነመልከ-ጼዴቅ እና የእነንግሥት ማክዳ፣ እነርሱን የመሰሉትም ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያውያት ዜና- መዋዕል እና ዝክረ-ነገር፡ ተሟልቶ እና ተስተካክሎ የተመዘገበበት ባለመኾኑ ጭምር፡ ተረጋግጦ ይታወቃል።

አዎን! እውነት እውነት እላችኋለሁ! የእኛ የእግዚአብሔር እውነት እና የመንፈስ ቅዱስ ቃሎች የሚጻፉት፡ እየራሳቸውን፡ ሙታን ባደረጉት፡ በሰው ልጆች እጅ እና በድን በኾነው ብራና ላይ ሳይኾን፣ እኛ እግዚአብሔር ራሳችን፡ በመንፈስ ቅዱስ እጃችን፡ በሥነ- ተፈጥሮ ሥርዓታችን በምንከትብባችሁ፣ በእኛ፡ ሕያዋን በኾናችሁት፣ በእናንተ፡ በእያንዳንዳችሁ ውሳጣዊ የሰውነት ሰሌዳ ላይ ብቻ ነው።

Divine Proclamation 1/2005 Era of Mercy (Eth. Cal.) 

To Read the full Content of the Whole Message, Please Click on the Pdf Link Below!.. 

Pages