ቍጥር ፲፪/፳፻፮ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ።

ቃለ ዐዋድ!
እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።

የአዋጅ ቃል!
ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

"ግብረ-ሰዶም" ተብሎ የተሰየመው፡ ፀያፍ የሙስና ግብር ያመጣው፥ የወንድና ወንድ፥ የሴትና ሴት ኢ-ተፈጥሮአዊ የኾነው፡ እስከጋብቻ ያደረሰ፡ ሰይጣናዊው የመወዳጀትና የሩካቤ-ሥጋ ግንኙነት፥ ፅንሰ-አሳቡና አኗኗሩን ጭምር በተመለከተ፡ እንዲሁም:  ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት፡ ሰዶሞችን በሚመለከት፡ ስላላት አቋም።

"ሕገ መንግሥቴ፡ በክርስትና ሃይማኖት ላይ የተመሠረተ ነው! የዚሁ ሕገ መንግሥቴ አመንጪዎችና አዘጋጆች፥ አጽዳቂዎችና ዐውዋጂዎች የኾኑት፡ የአገርነቴና የመንግሥትነቴ መሥራቾችም፡ ስለእውነተኛዋ የክርስትና እምነት ብለው፡ ከጨቋኞቹ፡ የአውሮጳ፡ የክርስቲያን አገሮች፡ የተሰደዱ ሰማዕታት ናቸው!" እያለች፡ በግብዝነት የምትመጻደቀው፡ "ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ" የምትባለው አገር፡ በዚህ ረገድ ያላትን የማንነትና የምንነት ባሕርይ፡ እስኪ፡ በጥቂቱ ጠለቅ ብላችሁ እንድትመለከቷት ላድርጋችሁ!

በነገረ ቀደም፡ እግዚአብሔር፡ ሰውን የፈጠረው፡ በአንድነት መልኩና በሥላሴነቱ አርአያ መኾኑን፥ ይኸውም፡ በነፍስና በሥጋ፥ በመንፈስም መኾኑን የማያውቅና የማያምን፥ በተለይ፡ ራሱን፡ ክርስቲያን ያደረገ ሰብኣዊ ፍጡር፡ በአኹኑ ጊዜ፡"ይኖራል!" ብላችሁ አታስቡ ይኾናል። ነገር ግን፡ እውነታው ይህ አይደለም።

ይህን መለኮታዊ ሕያው ሕንጻ የኾነውን፡ አንዱን ሰው ነው፡ ፩ኛ፡ ከሦስቱ አካላትና ባሕርያት መካከል፡ ሉዓላዊ የኾነው መንፈስ እንደሌለው፥ "በነፍስና በሥጋ" ብቻም እንደተፈጠረ፣ ፪ኛ፡ እነዚሁ ነፍስና ሥጋም፡ ከኹለት እንደተከፈሉ በመቁጠር፡ "ይህ፡ የሥጋ ነው! ይህ ደግሞ፡ የነፍስ ነው!" እያለች፡ እነዚያ፡ "ፍትሓ ነገሥት" የተባለው መጽሓፍ አዘጋጆች ካህናት፡ በ፬ኛው ምእት ዓመተ-ምሕረት፡ ለቄሣሩ ቆስጠንጢኖስ የሰጡትን ፀረ-እግዚአብሔርና ፀረ-ክርስቶስ፥ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ማርያም የኾነውን ሓሳዊ መመሪያ በማጽናት፡ የለያየችው፡ ይህችው፡ "ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ"፡ ናት።

ከዚሁ፡ ከ"ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ"፡ ስሑት አቋም የተነሣም፡ ከእርሷ ቀደምት ኾነው የተቋቋሙትን፡ የመሰሎቿን ሰብኣውያን መንግሥታት፡ ክፉና ጥፉ አርአያነት በመከተል፡ የእኛ፡ የፈጣሪ ብቸኛ ሀብት የኾነችውና በምሥጢረ ተዋሕዶ ሥላሴነታችን የተከወነችው፡ ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥታችን እንኳ ሳትቀር፡ መንፈሳዊ አገልግሎቷን፡ ለሕዝቦቻችን የምታበረክትባትን፡ የቤተ ክህነት ዘርፏን፡ ከቤተ-ሕዝቧና ከቤተ ምልክናዋ ለይታ በማስወገድ፡ "Church and State"፡ ማለትም፡ "ቤተ-ክህነት እና ቤተ-መንግሥት" ብላ፡ ከኹለት የከፈለችው፡ ይህችው፡ "ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ" ናት።

ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥታችን፡ "እኒህ ሰብኣውያን ፍጡሮቻችን፡ ሕይወታቸውን ጠብቀውና አንከባክበው፡ በመልካም እያካኼዱ ሊኖሩ የሚያስችላቸው፡ ተገቢውና እውነተኛው ሥርዓት፡ በዚህ፡ በእግዚአብሔራዊው የተዋሕዶ ሥላሴነታቸው ተፈጥሮ፡ ማለትም፡ በአንድነታቸውና በሦስትነታቸው ህላዌ ጸንተውና እርሱን ተከትለው ሲገኙ ብቻ ነው!" ስትል፡ ይህችው፡ "ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ" ግን፡ "የለም! አይደለም! እንዲህ ሳይኾን፡ በዲያብሎሳዊው ሰው-ሠራሽ ኹለትነት ተከፍለው ነው፡ ሊኖሩ፥ ሊካኼዱም የሚገባቸው!" እያለች ነው፡ በሓሳዊው ዕውቀቷ፥ ትምህርቷና ስብከቷ፥ በዕዳ በማሰነ ገንዘቧ፥ ቈሳቍሷና የጥበብ መሣሪያዋ፥ በኪነት በተራቀቀው፡ የምድር፥ የባሕርና የአየር ጦር ኃይሎቿ በመመካትና በመጠቀም፡ ይህን፡ የሓሳዊ መሲሕ ዓላማዋን እያወጀችና እያስፋፋች ያለችው።

መነሻውን ልታውቁት ከማይቻላችሁ ጊዜ አስቀድሞ ካለው እግዚአብሔርነታችን፥ እርሱም፡ የተባዕታይ [የወንድነት]፥ እና/ወይም፡ የአንስታይ [የሴትነት] ጾታ ከሌለው፡ ከዚሁ፡ ከአንዱው ራሳችን፡ በፍጹም ፈቃዳዊው ስምምነታችን፡ "እግዚአብሔር አብ እና እግዚአብሔር እም" ተብለን፡ በወንድነትና በሴትነት ጾታ፡ በእኩያነት ለኹለት ተከፍለን፡ አንዱን ተወዳጁን ልጃችንን፡ እግዚአብሔር ወልድን፡ ከፍጥረት መጀመሪያ በፊት፡ በመለኮታዊው አካላችንና ባሕርያችን፡ በፈጣሪ ማንነቱ፥ በኋላ ዘመን ደግሞ፡ በፍጥረት መጨረሻ፡ ከተዋሓድናት፡ ከድንግል ማርያም፡ በሰብኣዊው አካላችንና ባሕርያችን፡ ኢየሱስ መሲሕን፡ በፍጡር ምንነቱ እንደወለድነው፥ በእግዚአብሔር መንፈስ-ቅዱስነትም እንዳሠረፅነው ታውቃላችሁ።

እነዚህ "ሰዶሞች"፥ እናንተም ሰብኣውያን ፍጡሮቻችን ኹላችሁ፥ እያንዳንዳችሁ፡ እንዲህ፡ በወንድነትና በሴትነት ጾታዎች የተገኛችሁት፡ አስቀድሞ፡ "አዳም" ብለን የጠራነውን ሰብኣዊ ፍጡራችንን፡ እንደእኛው፡ የወንድነትና የሴትነት ጾታ ሳይኖረው፡ በአንድያው አርአያችንና ምሳሌያችን፡ አንድ አካልና አንድ ባሕርይ ብቻ አድርገን ከፈጠርነው በኋላ፡ ያንኑ፡ የአንድነት አካሉንና ባሕርዩን፡ እንደእኛው፡ እኩል ከፍለን፡ በወንድነትና በሴትነት ብልትና ጾታ፡ ተባዕትና አንስት አድርገን የሠራናቸው፡ እንደኛው፡ መሰሎቻቸውን፡ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን እየወለዱ፡ በመራባት እንዲበዙ፥ ምድሪቱንም መልተው እንዲኖሩባት ነው።

ጥያቄዎችና፡ መልስ ኾነው የተጠቃለሉት ዓበይት ቍም-ነገሮች
፩ኛ. ስለ"ግብረ-ሰዶም"፡ አጠያያቂው ነገር
፪ኛ. ግብረ-ሰዶም" ምንድር ነው?
፫ኛ. ግብረ-ሰዶም፡ እንዴት መጣ? ማንስ አመጣው? ለምንስ፡ እንዲህ ተስፋፍቶ፡ ከዚህ ደረጃ ደረሰ?
፬ኛ. ለግብረ-ሰዶም መፈጠር ዋና ምክንያቶች
፭ኛ. ለዚህ ጠንቀኛ ክፉ ችግር፡ መፍትሔው፡ ምንድር ነው?

መልእክቱን፡ በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...