ቍጥር ፲፯/፳፻፱ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ።

ቃለ ዐዋድ!

እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።

የአዋጅ ቃል!

ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

"እኔ: እግዚአብሔር ወልድ፡ ኢየሱስ መሲሕ፡ «'አቡነ ዘበሰማያት! የሰማያት አባታችን ሆይ!' በሚለው እና ደቀ-መዛሙርቴ፡ ጠይቀውኝ፡ ባስተማርኋቸው ጸሎት ውስጥ፡ ‹ሲሳየነ፡ ዘለለዕለትነ፣ ሀበነ ዮም! የየቀኑን ምግባችንን፡ ዛሬም ስጠን!› በሉ!» ያልሁበትን ምክንያት፡ በትክክልና በእርግጥ ታውቁት ዘንድ፡ አስፈላጊ ከኾነበት፡ ከመጨረሻው የሕይወት ዘመን ላይ ስለደረሳችሁ፡ ይህን እውነታ፡ ዛሬ፡ በዐዋጅ መልክ፡ ይኸው ላሳውቃችሁ፡ ፈቃዴ ኾነ!

በዚህ ረገድ የምላችሁን፡ ይህንኑ ቃሌን፡ እንግዴህ፡ በጽሙና ስሙኝ! ሰምታችሁኝም፡ በሃይማኖታዊ ምግባር ፈጽማችሁት፡ ለጣፋጩ ፍሬያማነቱ አብቁት! እርሱም፡ እንዲህ የሚል ነው፦ "እንኳንስ፡ የየዕለቱን ምግባችሁን ቀርቶ፡ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነቴ፡ እንድትኖርዋት እያደረግሁ ያለችውን፡ የቀኗን ሕይወታችሁን እንኳ፡ በህልውናችሁ ልትቀጥሉባት የቻላችሁት፡ በእኔ ነው።

ይህ ብሂሎቴ፡ "ወበከመ ዐጽቅ፡ ኢይክል ፈርየ ባሕቲቱ፣ እመ ኢሀሎ ውስተ ጕንደ ወይኑ፣ ከማሁ፡ ኢትክሉ ፈርየ፡ ለእመ ኢነበርክሙ ብየ! የወይን ቅርንጫፍ፡ ከግንዱ ከተገነጠለ፣ ብቻውን ሊያፈራ እንደማይችል ኹሉ፡ እናንተም፡ እንዲሁ፡ በእኔ ባትኖሩ፡ በህልውናችሁ ልትቀጥሉና ልታፈሩ አይቻላችሁም።" ከሚለው ቃሌ ጋር እንደሚስማማ፡ እናንተም አምናችሁበት፡ ተቀብላችሁታል። (ዮሓ. ፲፭፥ ፬።)

ጥያቄዎችና፡ መልስ ኾነው የተጠቃለሉት ዓበይት ቍም-ነገሮች
፩ኛ. በየቀኑ፡ እየሞታችሁ የምትነሡበት ትንግርት፡ 'የሞት ታናሽ ወንድም!" የምትሉት፡ እንቅልፍ
፪ኛ. ‹ሲሳየነ፡ ዘለለዕለትነ፣ ሀበነ ዮም! የየቀኑን ምግባችንን፡ ዛሬም ስጠን!› የሚለውን፡ ይህን ጸሎት፡ ዛሬም፡ በምውትነት ዓዘቅት፡ እየጸለዩት ያሉት፡ እነማን ናቸው?
፫ኛ. ‹ሲሳየነ፡ ዘለለዕለትነ፣ ሀበነ ዮም! የየቀኑን ምግባችንን፡ ዛሬም ስጠን!› የሚለውን፡ ይህን ጸሎት፡ ዛሬ፡ በአማናዊ ሕያውነቱ፡ እየጸለዩት ያሉትስ እነማን ናቸው?

መልእክቱን፡ በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...