አቡነ ዘበሰማያት፥ ጸሎት፥ እንቅልፍ፥ የቀን ምግባችንን፡ ዛሬም ስጠን። ፲፰ ግንቦት ፪ሺ፱ ዓም፥ ፪ሺ፱ ዓ.ም. (26 May 2017)

ቍጥር ፲፯/፳፻፱ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ።

ቃለ ዐዋድ!

እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።

የአዋጅ ቃል!

ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

መልእክቱን፡ በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...

 

ቍጥር ፲፯/፳፻፱ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ።

ቃለ ዐዋድ!

እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።

የአዋጅ ቃል!

ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

"እኔ: እግዚአብሔር ወልድ፡ ኢየሱስ መሲሕ፡ «'አቡነ ዘበሰማያት! የሰማያት አባታችን ሆይ!' በሚለው እና ደቀ-መዛሙርቴ፡ ጠይቀውኝ፡ ባስተማርኋቸው ጸሎት ውስጥ፡ ‹ሲሳየነ፡ ዘለለዕለትነ፣ ሀበነ ዮም! የየቀኑን ምግባችንን፡ ዛሬም ስጠን!› በሉ!» ያልሁበትን ምክንያት፡ በትክክልና በእርግጥ ታውቁት ዘንድ፡ አስፈላጊ ከኾነበት፡ ከመጨረሻው የሕይወት ዘመን ላይ ስለደረሳችሁ፡ ይህን እውነታ፡ ዛሬ፡ በዐዋጅ መልክ፡ ይኸው ላሳውቃችሁ፡ ፈቃዴ ኾነ!