ልደት፡ እግዚአብሔርታችን፡ እግዚአብሔራችን፡ ተአምረ ማርያም፡ ስንክሳር፡ ቀስተ ደመና፡ ጣዖት፡ ጽላት፡ ታቦት፡ ቃል ሥጋ ኾነ!፡ እሥራኤል፡ ምአ አንበሳ፡ ዘእምነገደ ይሁዳ!፡ ቄሣር፡ ንግሥት ሳባ፡ አቤሜሌክ ወይም ባኮሳ፡ መስከረም ፰ ቀን፥ ፪ሺ፱ ዓ.ም. (18 September 2016)

ከመስከረም ፩፡ ርእሰ-ዐውደ-ዓመት፡ እስከኅዳር ፳፩ ቀን፡ ተዝካረ-ማርያም ድረስ ስላሉ በዓላትና አጽዋማት፡ መልእክታዊ ማብራሪያ።

የእግዚአብሔር እም፡ ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደት።
[በግእዙ፡ "እግዝእትነ"፡ "እግዚአብሔርታችን" እንጂ፡ "እመቤታችን" ማለት አይደለም፤
"እግዚእነ"፡ "እግዚአብሔራችን" እንጂ፡ "ጌታችን" ማለት እንዳልኾነ።
Lord፡ "ጌታ"፥ Lady፡ "እመቤት" ተብሎ፡ እንደፈረንጆቹ ቋንቋ ሊተረጐም አይገባም።]

ከመስከረም ፩ ቀን፡ የርእሰ ዐውደ-ዓመት በዓል ጋር፡ ዐብሮ ስለሚታሰበው፡ ስለእግዚአብሔር እም፡ ድንግል ማርያም፡ የልደቷ በዓል፡ እዚህ ላይ፡ ሊታወስ የሚገባው ቍም-ነገር አለ። ያንንም፡ እንደሚከተለው ገላልጠን አቅርበንላችኋል፦

መልእክቱን በሙሉ ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...