ርእሰ ዐውደ ዓመት: ዕንቍጣጣሽ: ኢትዮጵያዊነት: ኤዶም ገነት: ደቂቀ እግዚአብሔር: ዓመተ-ኪዳን: መስከረም ፩ ቀን፡ ፪ሺ፲፫ ዓ.ም. (11 September 2020)

የ፪ሺ፲፫ (፳፻፲፫) ዓመተ ምሕረት፡ የዓውደ ዓመቱ: ምሥራች መልእክት።

ልዑል እግዚአብሔር፡ ከዘመነ ዮሓንስ፡ ወደዘመነ ማቴዎስ አሸጋግሮ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ኢትዮጵያን፡
የ፯ሺ፭፻፲ (የሰባት ሽህ አምስት መቶ ዐሥራ ሦስተ)ኛውን ዓመተ-ልደቷንና የነጻነት ህልውናችንን በዓል፣
እንዲሁም፡
የአዳምና የሔዋንን ልደት፥ የቅዱሱ ኪዳን፡ መነሻ የኾነው ሥርዓተ ጋብቻም የተከሠተበትን ቀን ያካተተውን፡ የፍጥረትን መገኛ ፯ሺ፭፻፲፫ኛውን ዓመት በዓል፥
ደግሞም፡ የእግዝእተብሔር እም፡ ድንግል ማርያምን፡ የ፪ሺ፳፱ (የኹለት ሽህ ዘጠነ)ኛውን ዓመት
እና
የእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕን፡ የ፪ሺ፲፫ (የኹለት ሽህ ዐሠራሦስተ)ኛውን ዓመት፡ የልደታት በዓል
ለማክበር ለበቃንበት፡ ለአዲሱ፡ የ፪ሺ፲፫ (፳፻፲፫)(ኹለት ሽህ ዐሥራሦስት፥ ወይም፡ ሃያ መቶ ዐሥራሦስት፥ ወይም፡ ዕሥራ ምእት ወዐሠርተሠለስቱ) ዓመተ-ምሕረት፥ መስከረም ፩ ቀን፣ እንኳን፡ በያለንበት፡ በሰላም አደረሰን!

መልእክቱን በሙሉ ለመመልከት፡ እንደሚከትለው ይቀጥሉ!...