ርእሰ ዐውደ ዓመት: ዕንቍጣጣሽ: ኢትዮጵያዊነት: ኤዶም ገነት: ደቂቀ እግዚአብሔር: ዓመተ-ኪዳን: ጷጉሜ ፭ ቀን፡ ፪ሺ፲፫ ዓ.ም. (10 September 2021)

የ፪ሺ፲፬ (፳፻፲፬) ዓመተ ምሕረት፡ የዓውደ ዓመቱ: ምሥራች መልእክት።

ልዑል እግዚአብሔር፡ ከዘመነ ማቴዎስ፡ ወደዘመነ ማርቆስ አሸጋግሮ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ኢትዮጵያን፡
የ፯ሺ፭፻፲፬ (የሰባት ሽህ አምስት መቶ ዐሥራአራተ) ኛውን ዓመተ-ልደቷንና የነጻነት ህልውናችንን በዓል፣
እንዲሁም፡
የአዳምና የሔዋንን ልደት፥ የቅዱሱ ኪዳን፡ መነሻ የኾነው ሥርዓተ ጋብቻም የተከሠተበትን ቀን ያካተተውን፡ የፍጥረትን መገኛ ፯ሺ፭፻፲፬ኛውን ዓመት በዓል፥
ደግሞም፡ የእግዝእተብሔር እም፡ ድንግል ማርያምን፡ የ፪ሺ፴ (የኹለት ሽህ ሰላሳ)ኛውን ዓመት
እና
የእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕን፡ የ፪ሺ፲፬ (የኹለት ሽህ ዐሠራአራት)ኛውን ዓመት፡ የልደታት በዓል
ለማክበር ለበቃንበት፡ ለአዲሱ፡ የ፪ሺ፲፬ (፳፻፲፬) (ኹለት ሽህ ዐሥራአራት፥ ወይም፡ ሃያ መቶ ዐሥራአራት፥ ወይም፡ ዕሥራ ምእት ወዐሠርተዐርባእቱ) ዓመተ-ምሕረት፥ መስከረም ፩ ቀን፣ እንኳን፡ በያለንበት፡ በሰላም አደረሰን!

መልእክቱን በሙሉ ለመመልከት፡ እንደሚከትለው ይቀጥሉ!...