ርእሰ ዐውደ ዓመት: ዕንቍጣጣሽ: ኢትዮጵያዊነት: ኤዶም ገነት: ደቂቀ እግዚአብሔር: ዓመተ-ኪዳን: ፪ ጳጉሜ ፪ሺ፰ ዓ.ም. (07 Sep. 2016)

የ፪ሺ፱ (፳፻፱) ዓመተ ምሕረት፡ የዓውደ ዓመቱ: ምሥራች መልእክት።

ልዑል እግዚአብሔር፡
ከዘመነ ዮሓንስ፡ ወደዘመነ ማቴዎስ አሸጋግሮ፡
የእግዚአብሔር መንግሥት ኢትዮጵያን፡
የ፯ሺ፭፻፱ (የሰባት ሽህ አምስት መቶ ዘጠኝ)ኛውን ዓመተ-ልደቷንና የነጻነት ህልውናችንን በዓል፣
እንዲሁም፡
የአዳምና የሔዋንን ልደት፥ 
የቅዱሱ ኪዳን፡ መነሻ የኾነው ሥርዓተ ጋብቻም የተከሠተበትን ቀን ያካተተውን፡
የፍጥረትን መገኛ ፯ሺ፭፻፱ኛውን ዓመት በዓል፥ 
ደግሞም፡ 
የእግዚአብሔር እም፡ ድንግል ማርያምን፡ 
የ፪ሺ፳፭ (የኹለት ሽህ ሃያ አምስት)ኛውን ዓመት 
እና 
የእግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ መሲሕን፡ 
የ፪ሺ፱ (የኹለት ሽህ ዘጠኝ)ኛውን ዓመት፡ 
የልደታት በዓል ለማክበር ለበቃንበት፡ 
ለአዲሱ፡ የ፪ሺ፱ (፳፻፱) (ኹለት ሽህ ዘጠኝ፥