ሰሙነ ሕማማት፥ ሥርዓተ ጸሎት፥ ሆሣዕና በአርያም፥ ሰው ሠራሽ ሥርዓት፥ የፋሲካ ራት፥ ምሥጢረ ቍርባን፥ ክህነት ሥርዓታት፥ ኅብስተ አኰቴት፥ ጽዋዓ በረከት፥ ጉልባን፥ በርባን፥ ሰፍነግ፥ ቅዳሜ ስዑር፥ መለኮታዊ ዐዋጅ፥ እብኖዲ፥ ታዖስ፥ ማስያስ፥ አማኑኤል፥ ትስቡጣ። ሚያዝያ ፪ ቀን፡ ፪ሺ፲፩ ዓ.ም. (10 April 2019).

የ፪ሺ፲፩ ዓመተ ምሕረት የሕማማት መልእክትና ሥርዓተ ጸሎት።

ፈጣሪያችንና አምላካችን ኢየሱስ መሲሕ፡ ምንጊዜም ከማትለየው፡ ከእግዝእተብሔር ቅድስት እናቱና እናታችን ድንግል ማርያም ጋር፡ አስቀድሞ፡ በዓለ-ኢትዮጵያን፥አከታትሎም፡ ተዝካረ-ኪዳነ ምሕረትንና ዓቢይ-ጾምን አስፈጽሞ፡ ለዘንድሮው በዓለ-ሆሣዕናና ዝክረ-ሰሙነ ሕማማት፡ እንኳን፡ በያለንበት፡ በደኅና አደረሰን!