ሱባዔ ጳጉሜ። ጳጉሜ ፩ ቀን፥ ፳፻፲ ዓ.ም. (6 September 2018)

ሱባዔ ጳጉሜ።

እኛ፡ የቅዱሱ ኪዳን የኢትዮጵያ ልጆች፡ "ሱባዔ ፍልሰታ" ካበቃች በኋላ፡ ኹለት ሳምንቶችን፡ በሥጋዊውና በመንፈሳዊው የፋሲካ ደስታና የሓሤት ድግስ ቆይተን፡ "ሱባዔ ጳጉሜ"፥ ወይም፡ "የጳጉሜ ሱባዔ" ብለን፡ ከሌሎቹ የዓመቱ አጽዋማታችን መካከል፡ አንዲቱ ኾና የምታስተናግደን፡ ትንሿ ሰሞን ትቀበለናለች። እርሷም፡ በመስከረም ፩ ቀን ለሚውለው፡ ለታላቁ የዐውደ ዓመት በዓላችን፡ ሰሙነ ዋዜማ የኾነችው፡ የዓመቱ መደምደሚያ ጾማችን እና ሱባዔያችን ናት።

መልእክቱን ለመከታተል፡ እንደሚከተለው ይቀጥሉ!...