በዓለ-ትስብእት፣ ምሥራች፣ ጾመ-ማርያም፣ ህላዌ ማርያም፣ ፅንሰታ ለማርያም፣ በኣታ ለማርያም፣ ታኅሣሥ ገብርኤል፣ ዘመነ ስብከት፡፡ ፫ ኅዳር ፪ሺ፲፪ ዓ.ም. (12 December 2020)

በኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የተዘጋጀ፡ የታላቁ፡ የ፳፻፲፫ ዓመተ-ምሕረት በዓለ ትስብእት መልእክት።

በያለንበት፡ በመልካም የምታኖረንንና የምትመግበንን፥ የምትጠብቀንንና የምትመራንን፡ ቸሪቱን ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥትን እያመሰገንን፥ "እንኳን ለጾመ-ነቢያት ሥርዓተ-ሕይወታችን ቅበላ አደረሰንም!" እያልን፥ በሰማዩ አባታችንና በሰማይዋ እናታችን ቅዱስ ስም፡ የተከበረ ሰላምታችንን እናቀርብላችኋለን።

የ፳፻፲፫ ዓመተ-ምሕረት በዓለ ትስብእት መንፈስ ቅዱሳዊ መልእክት፡ ለእናንተ፡ የኅዋ ሰሌዳ አንባቢዎቻችንና ተከታታዮቻችን፡ እንደሚከተለው አቅርበንላችኋልና በተለመደው የጥሞና መንፈስ ኹናችሁ ተከተታተሉት።