ነሐሴ ፳፭ ቀን፥ ፳፻፯ ዓ.ም. (31 August 2015)

ጾመ ጳጉሜ

"ጾመ ጳጉሜ"

     እኛ፡ የቅዱሱ ኪዳን የኢትዮጵያ ልጆች፡ "ጾመ ፍልሰታ" ካበቃች በኋላ፡ ኹለት ሳምንቶችን፡ በሥጋዊውና በመንፈሳዊው የፋሲካ ደስታና የሓሤት ድግሥ ቆይተን፡ "ጾመ ጳጉሜ"፥ ወይም፡ "የጳጉሜ ጾም" ብለን፡ ከሌሎቹ የዓመቱ አጽዋማታችን መካከል፡ አንዲቱ ኾና የምታስተናግደን፡ ትንሿ ሰሞን ትቀበለናለች። እርሷም፡ በመስከረም ፩ ቀን ለሚውለው፡ ለታላቁ የዐውደ ዓመት በዓላችን፡ ሰሙነ ዋዜማ የኾነችው፡ የዓመቱ መደምደሚያ ጾማችን ናት።

"ጳጉሜ" ምን ማለት ነው?