የባሮክ ሁሴን ኦባማ፡ የይፋ ጕብኝት፡ በኢትዮጵያ። ሓምሌ ፲፱ ቀን፥ ፳፻፯ ዓ.ም. (26 July 2015)

የአሜሪካው ርእሰ ብሔር፡ ባሮክ ሁሴን ኦባማ፡ በኢትዮጵያ ስላደረጕት፡ የይፋ ጕብኝት በተመለከተ፡ የተላለፈ መልእክት።

ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

ይድረስ፦ ለቅዱሱ ኪዳን፡

"የእግዚአብሔር እና የኢትዮጵያዋ ድንግል ማርያም ልጆች!"

እየራሳችሁን፡ ለዚህ ታላቅ ኪዳናዊ ጸጋ እንደምታበቁ ለታመነባችሁ፡
ለተወደዳችሁ አንባቢዎቻችንም!

አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ርእሰ ብሔር፡
በክቡር አቶ ባሮክ ሁሴን ኦባማ አማካይነት፡
በ"ኢትዮጵያ" ምድር፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረገውን፡ የይፋ ጕብኝት በሚመለከት፡
የተላለፈላችሁ መልእክት።

+ + +

በእግዚአብሔር አብወእም፥ ወወልድ፥ ወመንፈስ ቅዱስ ስም፡
ኢትዮጵያዊ ሰላምታችንን፡ በያላችሁበት እናቀርብላችኋለን።

የ"ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት"
ማንነትና ምንነት፡ ባጭሩ።