የታላቁ ዐውደ ዓመት በዓል ምንባባትና መዝሙራት።

የታላቁ ዐውደ ዓመት በዓል ምንባባትና መዝሙራት።

መስከረም አንድ ቀን፡ በርእሰ ዓውደ ዓመት፥
በድንግል ማርያም፡ በእናቲቱ ልደት፥
በኢየሱስ ክርስቶስ፡ ባምላክ ልጇም ትስብእት፥
የተወረሰውን ዓመተ ምሕረት፥
በአዳምና ሔዋን፥ የዓለሙን ፍጥረት፥
በቅዱሱ ኪዳን፡ የኢትዮጵያን ነጻነት፥
የተላበሱባት፡በእግዚአብሔርዋ መንግሥት፥
የኢትዮጵያ ሰዎች፥ ደግሞም ኢትዮጵያውያት፥
ባሉበት ቦታና በኑሮአቸው ዓይነት፥
በግል፥ በቤተሰብ፥ በኅብረተሰብነት፥
ቤተ ክርስቲያናቸው፡ መካነ ኪዳናት፥
በቅዱሱ መንፈስ፥ በተሰበሰቡበት፥
የመስቀል ማኅተም፡ ኾኗቸው አብነት፥
በ፬ቱ ማዕዘናት በሚፈጸም ሥርዓት፥
በታላቁ በዓል፡ ግጻዌው ወጥቶለት፥
የምስጋናን መሥዋዕት፡ ያቅርቡበት በእውነት።