የኢትዮጵያ ልጆች፥ የእግዚአብሔር ልጆች ሰባቱ ቅዱሳት ኪዳናት፥ ቤተ-መቅደስ፥ ድንግል ማርያም፥ መድኅን፥ መድኃኒት፥ የሃይማኖት ጸሎት፥ የቃል ኪዳን ጸሎት፥ የምስጋና ጸሎት፥ የሰላምታ ጸሎት፥ የታማኝነት ማረጋገጫ ቃል። መስከረም ፬ ቀን፥ ፪ሺ፱ ዓ.ም. (14 September 2016)

ቍጥር ፲፭/፳፻፰ ዓ. ም. ቃለ-ዐዋድ።

ቃለ ዐዋድ!
እምኢትዮጵያ፡ ዘመንግሥተ እግዚአብሔር።

የአዋጅ ቃል!
ከኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት።

በቅዱሱ ኪዳን፡ ኪዳናውያን ኢትዮጵያውያንና ኪዳናውያት ኢትዮጵያውያት፡ የቃል ኪዳን ልጆች ስለመሆነቸው፡ እነርሱን በተመለከተ፡ በእኛ (ኢትዮጵያ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት - ድንግል ማርያም) ዘንድ ያለውን ዐሳብ፡ ለፍጥረተ-ዓለም ማሳወቅን በተመለከተ።